መዝሙር 117 (NASV)

መዝሙር 117
1አሕዛብ117፥1 በዚህ ምንባብ አሕዛብ የሚለው ሕዝቦችን ያመለክታል። ሁላችሁ፤ እግዚአብሔርን አመስግኑት፤
ሕዝቦችም ሁሉ፤ ወድሱት፤
2ምሕረቱ በእኛ ላይ ታላቅ ነውና፤
እግዚአብሔርም ታማኝነት ለዘላለም ነው።
ሃሌ ሉያ።117፥2 ትርጕሙ እግዚአብሔር ይመስገን ማለት ነው።