መዝሙር 126 (NASV)

መዝሙር 126
መዝሙረ መዓርግ።
1 እግዚአብሔር የጽዮንን ምርኮ126፥1 ወይም እግዚአብሔር ሀብቷን ይመልሳል። በመለሰ ጊዜ፣
ሕልም እንጂ እውን አልመሰለንም።126፥1 ወይም የሰዎቿ ጤንነት ይታደሳል።
2በዚያ ጊዜ አፋችን በሣቅ፣
አንደበታችንም በእልልታ ተሞላ፤
በዚያ ጊዜም በሕዝቦች መካከል፣
እግዚአብሔር ታላቅ ነገር አደረገላቸው” ተባለ።
3 እግዚአብሔር ታላቅ ነገር አደረገልን፤
እኛም ደስ አለን።
4 እግዚአብሔር ሆይ፤ በኔጌብ እንዳሉ ጅረቶች፣
ምርኳችንን መልስ።126፥4 ወይም ሀብታችንን መልስ
5በእንባ የሚዘሩ፣
በእልልታ ያጭዳሉ።
6ዘር ቋጥረው፣
እያለቀሱ የተሰማሩ፣
ነዷቸውን ተሸክመው፣
እልል እያሉ ይመለሳሉ።