መዝሙር 120 (NASV)
መዝሙር 120
መዝሙረ መዓርግ።
1በተጨነቅሁ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ተጣራሁ፤
እርሱም መለሰልኝ።
2 እግዚአብሔር ሆይ፤ ከሐሰተኛ ከንፈር፣
ከአታላይ ምላስም አድነኝ።
3ሐሰተኛ አንደበት ሆይ፤ ምን ይከፈልህ?
ከዚህስ የባሰ ምን ይደረግብህ?
4በተሳለ የጦረኛ ቀስት፣
በግራር ከሰል ፍም ይቀጣሃል።
5በሜሼኽ እኖራለሁና፣
በቄዳር ድንኳኖች መካከል እቀመጣለሁና ወዮልኝ!
6ሰላምን በሚጠሉ መካከል፣
ነፍሴ እጅግ ብዙ ጊዜ ኖረች።
7እኔ የሰላም ሰው ነኝ፤
እነርሱ ግን በተናገርሁ ጊዜ ጦርነትን ይሻሉ።