መዝሙር 16 (NASV)
መዝሙር 16
የዳዊት ቅኔ በሚክታም16፥0 በሙዚቃ ውስጥ የሚጠቀሙበት ቃል ሳይሆን አይቀርም።።
1አምላክ ሆይ፤ መጠጊያዬ ነህና፣
በከለላህ ሰውረኝ።
2 እግዚአብሔርን፣ “አንተ ጌታዬ ነህ፤
ከአንተ በቀር በጎነት የለኝም” አልሁት።
3በምድር ያሉ ቅዱሳን፣
ሙሉ ደስታ የማገኝባቸው ክቡራን ናቸው።16፥3 ወይም በምድሪቱ ላሉ አረማውያን፣ ካህናትና ደስ ለተሠኙባቸው መኳንንት ሁሉ ይህን እላለሁ
4ሌሎችን አማልክት የሚከተሉ፣
ሐዘናቸው ይበዛል፤
እኔ ግን የደም ቍርባናቸውን አላፈስስም፤
ስማቸውንም በአፌ አልጠራም።
5 እግዚአብሔር የርስት ድርሻዬና ጽዋዬ ነው፤
ዕጣዬም በእጅህ ናት።
6መካለያ ገመድ ባማረ ስፍራ ተጥሎልኛል፤
በርግጥም የተዋበች ርስት አግኝቻለሁ።
7የሚመክረኝን እግዚአብሔርን እባርካለሁ፤
በሌሊት እንኳ ልቤ ቀናውን ያመላክተኛል።
8 እግዚአብሔርን ሁልጊዜ በፊቴ አድርጌአለሁ፤
እርሱ በቀኜ ስላለ አልናወጥም።
9ስለዚህ ልቤ ደስ አለው፤ አንደበቴም ሐሤት አደረገ፤
ሥጋዬም ያለ ሥጋት ዐርፎ ይቀመጣል፤
10በሲኦል16፥10 ወይም በመቃብር አትተወኝምና፤
በአንተ የታመነውም16፥10 ወይም በአንተ የታመነውን መበስበስን እንዲያይ አትፈቅድም።
11የሕይወትን መንገድ ታሳየኛለህ፤16፥11 ወይም ታሳውቀኛለህ
በአንተ ዘንድ የደስታ ሙላት፣
በቀኝህም የዘላለም ፍሥሓ አለ።