መዝሙር 121 (NASV)

መዝሙር 121
መዝሙረ መዓርግ።
1ዐይኖቼን ወደ ተራሮች አነሣሁ፤
ረድኤቴ ከወዴት ይመጣል?
2ረድኤቴ ሰማይንና ምድርን ከፈጠረ፣
ከእግዚአብሔር ዘንድ ይመጣል።
3እግርህ እንዲሸራተት አይፈቅድም፤
የሚጠብቅህም አይተኛም።
4እነሆ፤ እስራኤልን የሚጠብቅ አይተኛም፤
አያንቀላፋምም።
5 እግዚአብሔር ይጠብቅሃል፤
እግዚአብሔር በቀኝህ በኩል ይከልልሃል።
6ፀሓይ በቀን አያቃጥልህም፤
ጨረቃም በሌሊት ጕዳት አታመጣብህም።
7 እግዚአብሔር ከክፉ ሁሉ ይጠብቅሃል፤
ነፍስህንም ይንከባከባታል።
8 እግዚአብሔር ከአሁን ጀምሮ እስከ ዘላለም፣
መውጣትህንና መግባትህን ይጠብቃል።

Topics in this chapter